Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 46 በመቶ ቅናሽ አሳየ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 46 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን የተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ጉባኤ (ዩኒታድ) አስታወቀ።
 
ጉባኤው ትልቁ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ቅናሽ ያጋጠመው ባደጉ ሀገራት ውስጥ ሲሆን ሁሉንም አይነት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት አቋርጧል ብሏል።
 
ዓለም አቀፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቱ ከፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር 2019 ጋር ሲነፃፀር በ2020 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 49 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
 
ለውጭ የቀጥታ ኢንቨስትመንት መውደቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ያሳደረው ተፅዕኖ ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል ተብሏል።
 
የኮሮና ቫይረስ በተከሰተበት ወቅት በዓለም ላይ እንቅስቃሴዎች መገደባቸው የነበሩትን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እድገት አዝጋሚ እንዳደረገው ተጠቁሟል።
 
እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ያስከተለው ከባድ የኢኮኖሚ ውድቅት ዓለም አቀፍ ኢንተርፕራይዞች ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ አድርጓልም ነው የተባለው።
 
የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይ ባደጉ ሀገራት ከተገመተው በላይ ከባድ ተፅዕኖ እንደነበረው የተገለፀ ሲሆን በአዳጊ ሀገራት ላይ በ2020 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያሳደረው ተፅዕኖ በአንፃራዊነት የተሻለ እንደነበረም የተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ጉባኤ ገልጿል።
 
በዚህም መሰረት ያደጉ ሀገራት በስድስት ወራት ውስጥ 98 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ማጣታው የተነገረ ሲሆን ከ2019 ሲነፃፀር በ75 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
 
በታዳጊ ሀገራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት 16 በመቶ ቢሆንም ከተጠቀበው በታች መሆኑን መረጃው አመልክቷል።
 
በተለይ ቻይና ከተፅዕኖው በፍጥነት ማገገሟ በታዳጊ ሀገራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ቅናሽ በተገመተው ልክ እንዳይቀንስ ያደረገ ምክንያት ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.