Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በምዕራብ ሸዋ በክላስተር የለማን የበቆሎ ማሳ ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በሁለተኛ ቀን የስራ ጉብኝት በምዕራብ ሸዋ በክላስተር የለማን የበቆሎ ማሳ ጎብኝቷል።

በዞኑ 88 ሺህ ሄክታር መሬት የበቆሎ ማሳ በክላስተር እየለማ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም 612 ሺህ 490 መሬትም በተለያዩ ምርቶች የተሸፈነ ሲሆን፥ 22 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተገለጸው።

አቶ ሽመልስ ከዚህ ቀደም 300 ሺህ ሄክታር መሬት ብቻ ይሸፍን የነበረው የኩታ ገጠም እርሻ አሁን ላይ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሸፈኑን በመጥቀስ ለአርሶ አደሮች እና የግብርና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም ከዚህ ቀደም ለቢራ ገብስ ይወጣ የነበረውን እስከ 200 ሚሊየን ዶላር ማስቀረት መቻሉንም አንስተዋል።

በዘንድሮው የምርት ዘመንም በ600 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የስንዴ ምርት በማምረት በዓመት ይወጣ የነበረውን እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ጎሮ ወረዳ አዳሚ ወዴሳ ቀበሌ በክላስተር የለማን የጤፍ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡

በአፈወርቅ አለሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.