Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ባለሃብቶች የሚያጋጥማቸውን ማነቆ ለመፍታት የተቋቋመው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ባለሃብቶች የሚያጋጥማቸውን ማነቆ ለመፍታት የተቋቋመው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ።

በመድረኩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ግርማ ብሩ ተገኝተዋል።

በስብሰባው የውጭ ባለሀብቶች በሀገሪቱ እያደረጉ ባለው የኢንቨስትመንት እንቅስቀሴ እያጋጠሙ ያሉ ማነቆዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ አማካኝነት በሀገሪቱ መዋዕለ ነዋያቸውን እያፈሰሱ ያሉ ሁለት ኩባንያዎች ያጋጠማቸው ተግዳሮቶችን በተመለከተ የማሳያ የዳሰሳ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አጠቃላይ ሁኔታን በተመለከተ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ውይይት ተደርጓል።

በጽሁፍም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ነባራዊ ሁኔታና የኮቪድ-19 ተጽዕኖ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡

በመጨረሻም ውይይቱን ተከትሎ በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ላይ አቅጣጫ መቀመጡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በውይይቱ ላይ ከብሄራዊ ባንክ፣ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከማዕድን ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ እና ከሌሎች መስሪያ ቤቶች የመጡ ሚኒስትሮች እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.