Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በሸበሌ ወንዝ ላይ የተገነባውን የጎዴ የመስኖ ግድብ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሸበሌ ወንዝ ላይ የተገነባውን የጎዴ የመስኖ ግድብ ጎበኙ።

በጉብኝቱ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ጉብኝቱን አስመልክቶ፥ “በሸበሌ ወንዝ ላይ የተገነባውን የጎዴ የመስኖ ግድብ ጎብኝተናል” ብለዋል።

በግድቡ አማካኝነት 2 ሺህ ሄክታር የቆላማ አካባቢዎች የግብርና ስራ አካል የሆነው የስንዴ ሰብል መልማቱንም አስታውቀዋል።

ከስንዴ በተጨማሪ የአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም የቅባት እህሎች በስፋት የሚመረቱ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.