Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጋምቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት በኢትዮጵያ የጋምቢያ አምባሳደር ሱሌማን አልዩ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

በወቅቱም አቶ ገዱ አምባሳደር ሱሌማን የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

የሁለቱን አገራት ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር መስራት እንደሚያስፈልግም አቶ ገዱ አንስተዋል።

ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ እየተደረገ ያለውን ድርድር በተመለከተም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል።

አምባሳደር ሱሌማን አልዩ በበኩላቸው÷ አፍሪካዊያን የአፍሪካን ችግር በራሳቸው ለመፍታት የሚያስችል አቅም ማዳበራቸውን ገልጸዋል።

ጋምቢያ ለአፍሪካዊያን ሉዓላዊነት ትልቅ ዋጋ ትሰጣለችም ነው ያሉትአምባሳደሩ÷በኢትዮጰያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥም አድንቀዋል።

አምባሳደር ሱሌማን አያይዘውም ሁለቱ አገሮች ትብብራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ በሚያስችሉ እንደ ቱሪዝም እና የካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ላይ አትኩረው መስራት እንዳለባቸውም ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.