Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታህሳስ 3 ቀን ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 3 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ አስታወቀ፡፡
ውድድሩ በዲ ኤስ ቲቪ በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን ውድድሩን የሚያስተላልፍ የባለሙያዎች ቡድን ለቅድመ ዝግጅት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
ቡድኑ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ በሀገሪቱ የሚገኙ ስታዲየሞችን ተዘዋውሮ ይጎበኛልም ነው ያለው፡፡
የፊታችን እሁድም ወደ ባህር ዳር በማቅናት የባህር ዳር ስታዲየምን እንደሚጎበኝ ከኩባንያው የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.