Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ነባሩንና አዲሱን የሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ነባሩንና አዲሱን ሐሰተኛ የገንዘብ ኖት መያዙን አስታወቀ፡፡

ፖሊስ ነባሩን የገንዘብ ኖት ከሁለት ተጠርጣሪዎች ሐሰተኛ የሆነ ባለ መቶና ባለ አምሳ 174 ሺህ 350 ብር ይዟል፡፡

ከአንድ ግለሰብ ደግሞ ከ200 ሺህ በላይ ሐሰተኛ አዲሱ ባለ መቶና ባለ ሁለት መቶ የብር ኖት መያዙን ነው የገለጸው፡፡

እንዲሁም ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት 14 ሺህ 800 ሐሰተኛ ባለ መቶና ባለ ሃምሳ የአሜሪካ ዶላር ይዟል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ የህገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጥበቡ በሐሰተኛ ነባሩ የብር ኖት አንድ የክስ መዝገብ እንዲሁም በሐሰተኛ አዲሱ የብር ኖት ደግሞ አራት የክስ መዝገቦችን በመክፈት እያጣራ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.