Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን አገለሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ማግለላቸው ተገለፀ።
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ በቅርበት ያገኙት ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ስለተረጋገጠ ራሳቸውን አግልለዋል።
በአሁኑ ሰዓትም ጤናቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እና ምንም አይነት የቫይረሱ ምልክት እንደሌለባቸውም አስታውቀዋል።
ሆኖም ግን በዓለም ጤና ድርጅት ፕሮቶኮል መሰረት ለቀጣይ ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ ያስታወቁት ዶክተር ቴድሮስ፥ ስራቸውንም ቤታቸው ሆነው
እንደሚሰሩ ነው ያስታወቁት።
ምንጭ፦ aljazeera.com
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.