Fana: At a Speed of Life!

የደህንነት ተቋማት በፖለቲካ ሽግግሩ ውስጥ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደህንነት ተቋማት በሀገሪቱ የፖለቲካ ሽግግር ላይ ያላቸውን ሚና የተመለከተ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በስትራቴጅክ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በሃያት ሪጀንሲ እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ላይ የደህንነት ተቋማት እና የዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

የባለሙያዎች እና የጥናት እጥረት፣ ለውጥን የመቀበል ችግር እና ሙስና በደህንነት ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል።

በሴሚናሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የደህንነት ተቋማት ባለፉት ሁለት ዓመታት በለውጥ ሂደት ውስጥ ማለፋቸውን ገልፀዋል።

ለውጡም ያስፈለገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩ እና በዘርፉ የክህሎት እጥረት በመስተዋሉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሌተናል ጄኔራል ገብረፃድቃን ገብረትንሳይ በበኩላቸው በደህንነት ተቋማት አሰራር ላይ ውጤታማነት ፣ ብቃት ፣ ህጋዊነት እና ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ አብራርተዋል።

የደህንነት ተቋማት በፖለቲካ ሽግግር ውስጥ ስራቸውን በብቃት ማከናወን እንዲችሉ በፖሊሲ መደገፍ እና ዘላቂ ስረዓትን መገንባት እንደሚያስፈልግም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል።

ተሳታፊ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው የደህንነት መዋቅሩ  ከኢኮኖሚ እና ከሌሎች ተቋማት እንደማይለይ በመግለፅ ብሄራዊ ለዉጡ ከደህንነት ተቋም ለውጥ ውጪ ሊሳካ አይችልም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.