Fana: At a Speed of Life!

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መቋቋም የሚችል የጤና ስርዓት የስልጠና ማንዋል ዝግጅት አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መቋቋም የሚችል የጤና ስርዓት የስልጠና ማንዋል ለማዘጋጀት አውደ ጥናት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
አውደ ጥናቱ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መልሶ ማቋቋም እና የሬዚሊየንስ ዳይሬክቶሬት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
የስልጠና ማንዋሉ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን በተሻለ መንገድ ለመቋቋም የጤና ስርዓቱን ዝግጁነት ለማጠንከር እና መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጊዜ ለመስጠት የሚያስችልና የሕብረተሰቡን የጤና አደጋዎች ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የተለያዩ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች በሚከሰቱ ሰዓት በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችል የጤና ስርዓት መገንባት አስፈለጊ ሆኖ በመገኘቱ ሁሉም የዓለም ሃገራት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የኢንስቲቲዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር የተለያዩ ልምዶች በመውሰድና በመጠቀም ለኢትዮጵያ፣ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ጠንካራ የጤና ስርዓት መገንባት የሚያስችል ሞጁል ማዘጋጀት ይገባልም ብለዋል፡፡
ከጤና ሚኒስቴር፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በአውደጥናቱ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
See Translation
0
People Reached
0
Engagements
Boost Unavailable
Like

Comment
Share

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.