Fana: At a Speed of Life!

ኤርዶኻን ቱርክ በተቻለ ፍጥነት ወታደሮችን ወደ ሊቢያ እንደምትልክ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ቱርክ በተቻለ ፍጥነት ወታደሮችን ወደ ሊቢያ እንደምትልክ አስታወቁ።

ሊቢያ ወታደራዊ ድጋፍ መጠየቋን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ ሃገራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ለሰጠው ለፋይዝ አል ሳራጅ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ወታደሮቿን ትልካለች ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ፓርላማው ወታደሮችን ወደ ሊቢያ የመላክ እቅድ ያጸድቀዋል ብለው እንደሚጠብቁም ጠቅሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ትናንት በቱኒዚያ ባደረጉት ጉብኝት ሃገራቸው ከሊቢያ ጥያቄ ከቀረበላት ወታደሮችን ለመላክ ፈቃደኛ ስለመሆኗ ገልጸው ነበር።

ከዚህ ባለፈም የጀኔራል ከሊፋ ሃፍታር ወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ሃገራቸው ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.