Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት በህወሃት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ከፌዴራል መንግስት ጎን ናቸው- አቶ ሙስጠፌ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት በህወሃት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ከፌዴራል መንግስት ጎን መሆናቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ገለፁ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት መግለጫ ህወሓት ኋላ ቀር፣ ከፋፋይ እና ዘረኛ ስርዓት በሀገሪቱ ላይ ዘርግቶ መቆየቱን ገልፀዋል።
በዚህም በሶማሌ ክልል ህዝብ እና በሀገር ሽማግሌዎች ላይ በተለያዩ ወቅቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀም እንደነበረ በመግለጫው አንስተዋል።
ህወሓት ከለውጡ በኋላም በሶማሌ ክልል በተለያዩ ብሄሮች እና የሃይማኖት ተከታዮች መካከል ግጭት በመፍጠር አካባቢው እንዳይረጋጋ ቢሰራም፤ በህዝቡና በክልሉ መንግስት ጥረት መክሸፉን ነው የተናገሩት።
ዛሬም ቢሆንም ትንኮሳው አይቀርም ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ይህን በመከላከል ለሀገር አንድነት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
አሁን ላይ ፋሽስታዊ አጀንዳው መቋጫ የሚያገኝበት እና ፍትህ የሚሰጥበት ጊዜ ላይ ተደርሷል ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.