Fana: At a Speed of Life!

ሕዝቡ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ የአማራ ክልል መንግስት ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሕዝቡ ሰላሙን እንዲያስጠብቅ የአማራ ክልል መንግስት ጥሪ አቀረበ።
ህወሓት ውስጥ ያለው የጥፋት ቡድን ላለፉት ዓመታት ያደረሰው በደል አልበቃ ብሎት በሀገር ላይ ጦርነት ከፍቷል አሉ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ፡፡
ዳይሬክተሩ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በሀገር ላይ ጦርነት ሲከፍት የአማራን ክልል ለማጥቃት ሙከራ ማድረጉን የጠቀሱት አቶ ግዛቸው፤ የመከላከያ ሰራዊቱና የክልሉ የፀጥታ ኃይል ጥቃቱን መክቷል ብለዋል።
የአማራ ክልል የመጀመሪያው የጥቃቱ ሰለባ ስለሆነ በተለየ ትኩረት ጠላቱን እንደሚመክት ተናግረዋል።
በህወሓት ውስጥ ያለው የጥፋት ቡድን የትግራይ ሕዝብም ጠላት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚደርሰው ጥቃት የቡድኑ እጅ አለበት ብለዋል፡፡
የህግ ማስከበሩ ሥራ ግቡ ቡድኑን ከጥፋት ሴራው ማስወገድ ነውም ነው ያሉት፡፡
በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ የአማራ ክልል የፌደራል መንግሥቱን እንደሚደግፍ አቶ ግዛቸው ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል በጥፋት ቡድኑ ላይ ህግ ለማስከበር እያደረገ ያለው ሥራ ስኬታማ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በሁለት ቀናት በነበረው ህግ የማስከበር ስራ ማኅበረሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ ማሳየቱን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
ሕዝቡ በጥንቃቄ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.