Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በገዳሪፍ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱዳን በገዳሪፍ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷ ተገልጿል።

ሱዳን በገዳሪፍ በኩል ያለውን ድንበር መዝጋት የጀመረችው የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት ውስጥ ባለ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ተከትሎ መሆኑም ታውቋል።

በምስራቅ ገዳሪፍ ግዛት የሚገኙ ባለስልጣኖች ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው ድንበር ከዛሬ ጀምሮ ዝግ መደረጉን ማስታወቃቸውም ተነግሯል።

ቀጣይ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስም ድንበሩ ዝግ ሆኑ እንደሚቆይ ማስታወቃቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት ያወጣው ዘገባ ያመላክታል።

ሱዳን በከሰላ ግዛት በኩልም ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ደንበር መዝጋቷ ይታወሳል።

የከሰላ ግዛት አስተዳዳሪ ፈታህ አል ራሀማን አል አሚን፥ ካሳለፍነው ሀሙስ ጀምሮ ሱዳን ከኢትዮጵያ ከምትዋሰንባቸው ድንበሮች አንዱ በሆነው ከሰላ ግዛት አካባቢ ያለው የድንበር ዝግ ተደርጓል ብለዋል።

በአካባቢው ያለው የፀጥታ ኃይል ድንበሩን በንቃት እንዲጠብቅና ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የጦር መሳርያ ይዞ ወደ ሱዳን እንዳይገባ እንዲያደርግ መታዘዙንም አስተዳዳሪው ፈታህ አልራሃማን መናገራቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.