Fana: At a Speed of Life!

ናይጄሪያ ከቻይና ለምታገኘው ብድር በሉዓላዊነቷ አልተደራደረችም- የሀገሪቱ ትራንስፖር ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ናይጄሪያ ከቻይና ጋር ከተፈራረመችው የ400 ሚሊየን ዶላር ብድር ጋር ተያያዞ ሉዓላዊነቷን አሳልፋ ሰጥታለች በሚል የቀረበባትን ከስ ውድቅ አድርጋለች።
በፈረንጆቹ 2014 ናይጄሪያ ከቻይናው ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ ጋር ብድሩን በተፈራረመችበት ወቅት ብድሩን መክፈል ካልቻለች ሉዓላዊነቷን አሳልፎ የሚሰጥ ሀሳብ ላይ ተፈራርማለች ተብሏል።
የህግ ባለሙያዎች መንግስት የተፈራረመውን ውል ይፋ እንዲያደርግ እየጠየቁ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ናይጀሪያ ሉዓላዊነቷን ለቻይና አሳልፋ ሰጥታለች የሚለውን ነገር ማመናቸው ተነግሯል።
የሀገሪቱ ትራንስፖርት ሚኒስትር ቺቡኬ አምቼ ነገሩ ይሄ አይደለም ብለዋል ለቢቢሲ በሰጡት አስተያየት።
ቻይናዎቹ ናይጄሪያ ብድሩን መክፈል ካልቻለች በስምምነቱ መሰረት ፍርድ ቤት እንሄዳለን ነው ያሉት ሲሉ የቀረበባቸውን ወቀሳ አጣጥለዋል።
ሚኒስትሩ ናይጄሪያ ብድሩን መክፈል ካልቻለች ቻይና አስተዳዳሪ ትሾማለች በሚል የስምምነቱን ሀሳብ በተሳሳተ መንገድ እንዲተረጎም አድርጓል ያሉትን ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆነውን ፒፕልስ ዴሞክራቲክ ፓርቲን ከሰዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.