Fana: At a Speed of Life!

ፊሊፒንስ ሁለት የአሜሪካ ሴናተሮችን  ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊሊፒንስ  ሁለት የአሜሪካ ሲናተሮችን ወደ ሀገሯ ለጉብኝት እንዳይገቡ ማገድዋ ተገለፀ፡፡

የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ   በቀጣይ ወደ ፊሊፒንስ በሚገቡ የአሜሪካ ዜጎች ጠንከር ያለ የመግቢያ እቀባ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ፊሊፒንስ  በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነቷ የምትታወቀውን  ሌይላ ዴ ሊማን ማሰሯን ተከትሎ አሜሪካ በዚህ ላይ የተሳተፉ አካላት ወደ  ሀገሯ እንዳይገቡ የሚያደርግ ውሳኔ ሀሳብ በሴናተሮች ቀርቧል፡፡

ይህ ውሳኔ ያስቆጣት ፊሊፒንሲም ሁለቱ የአሜሪካ ሴናተሮች ዲክ ዱርቢን እና ፓትሪክ ሌህይ ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ መወሰኗን ቃል አቀባዩ ሳልቫዶር  ፓኔሎ ተናግረዋል፡፡

በአሁን ወቅት ፊሊፔን ለአሜሪካውያን ለ30 ቀናት  የሚቆይ ከቪዛ ነፃ መግቢያ ፈቃድ መስጠቷ ነው የተነገረው፡፡፡

በማኒላ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እና የመንግስት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ ምንም የሰጠው ምላሽ የለም ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.