Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያንና የጀርመን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በሁርሶ ኮንቲጀት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያን እና የጀርመን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በሁርሶ ኮንቲጀት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የስላም ማሰከበር ማሰልጠኛ ተቋም አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ታምራት አንዳርጌ  እንደተናገሩት፥ የጉብኝቱ ትኩረት አዲስ የትራንስፖርት እና የጥገና ስራዎችን  ለማቋቋም፣ ማሰልጠኛውን ዘመናዊነቱን ጠብቆ ለማደስ እና አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው።

የጀርመን ወታደራዊ አታች ኮሎኔል ቶማስ  ሪበርሊንገ በበኩላቸው፥ ባደረግነው የመስክ ጉብኝት ቀጣይ ላቀድነው እና ለምንሰራቸው ስራዎቻችን ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልናል ብለዋል።

የጀርመን እና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ትብብርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.