Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 521 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 771 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ህዳር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ )ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 478 የላቦራቶሪ ምርመራ 521 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 101 ሺህ 248 ደርሷል።

በሌላ በኩል የዛሬውን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 63 ሺህ 268 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 554 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 36 ሺህ 424 ሰዎች መካከል 313 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 545 ሺህ 131 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.