Fana: At a Speed of Life!

ዲፕሎማቶች መንግስት በትግራይ እያካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ለሚመለከተው የዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ማስገንዘባቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዲፕሎማቲክ ተልዕኮ የስራ ሃላፊዎች ጋር በትግራይ ክልል እየተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻን በተመለከተ የዌቢናር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ የሚሲዮን ሃላፊዎች እንደተናገሩት፤ የህግ ማስከበር ዓላማውን በተመለከተ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
መንግስት የሚያካሂደው ዘመቻ የህወሃት ጁንታ እያስከተለ ያለውን ቀውስ ለማስቆምና የጁንታው አባላትን ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሆነ ለሚመለከታቸውና ወሳኝ ለሆኑ አካላት ማስገንዘባቸውን ገልጸዋል።
ዘመቻው የህግ የበላይነትን በማስጠበቅ፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረብና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን በማስጠበቅ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ስለመሆኑ የማስገንዘብ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ማረጋገጣቸው ተገልጿል፡፡
ለተለያዩ አገሮች መንግስታትም በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ እንደሚፈጥሩም ገልፀው÷ ይህንን ማድረጋቸውም መገናኛ ብዙሃን መሬት ላይ ያለውን እውነታ ተገንዝበው ሚዛኑን የጠበቀ ዘገባ ለመስራት እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።
ሚሲዮኖቹና ሚኒስቴሩ የተዛባ መረጃ እንዳይሰራጭም ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተገልጿል።
በትግራይ እየተካሄደ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ሲቪሎች እንዳይጎዱ ተገቢው ጥንቃቄ በማድረግ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ ከህወሃት ጁንታ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ለማህበረሰቡ የሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
የሚሲዮን ሃላፊዎችና ሁሉም ዲፕሎማቶች መንግስት በጁንታው ላይ የሚያካሂደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ለቀጣናዊና ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ የማስገንዘብ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ደመቀ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.