Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነትን የማስከበሩን ዘመቻ በብቃት ታጠናቅቃለች -ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነትን የማስከበሩን ዘመቻ በብቃት ታጠናቅቃለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
የሐሰተኛው አጥፊ ቡድን መጨረሻ ተቃርቧል በማለትም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በተለይም ባለፉት ቀናት የታዩት ሁኔታዎች በህወሓት ውስጥ ያለውን አጥፊ ቡድን ትክክለኛ ማንነት የገለጡ ናቸው ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ገልፀዋል።
የሕግ የበላይነትን በማስከበር እንዲሁም ኢትዮጵያን በመዝረፍና ሰላሟን በማወክ የተሠማሩትን ተጠያቂ በማድረግ፣ ለዘላቂ ሰላም የሚሆን ጠንካራ መሠረት እንገነባለን ነው ያሉት።
በዚህም በሰብአዊነት እና በሰላም ላይ ወንጀል የፈጸሙ ሁሉ ተጠያቂዎች እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡
ፍትሕ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ባለን ውሳኔ በቆራጥነት እንገሠግሳለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴቶች እና በወንዶች ልጆቿ ጽናት እና ቆራጥነት፣ ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነትን የማስከበሩን ዘመቻ በብቃ ታጠናቅቃለች ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.