Fana: At a Speed of Life!

የህብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦ ድሬዳዋ ገባ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ15ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል መገለጫ የሆነው የህብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦ ድሬዳዋ አስተዳደር ገባ።

በሀረሪ ክልል የቆየው የህብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦ ዛሬ ድሬዳዋ ገብቷል።

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አዲስዓለም በዛብህ ችቦውን ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋጡማ ሙስጠፋ አስረክበዋል።

በአቀባበል በስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የካቢኔ አባላት፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።

ችቦው በድሬዳዋ ለሁለት ቀናት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ አፋር ክልል አሸኛኘት እንደሚደረግለት ኢዜአ ዘግቧል።

የዘንድሮ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “እኩልነትና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.