Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር ከሴት አመራሮች፣ የሰላም እናቶችና አደ ስንቄዎች ጋር ምክክር እያደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 7 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ከተወጣጡ የሴት አመራሮች፣ የሰላም እናቶችና አደ ስንቄዎች ጋር በአዳማ ከተማ ምክክር እያደረገ ነው።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰላም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ወይዘሮ አስማ ረዲ÷ መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር በ2013 ዓ.ም ከሚያካሂዳቸው ማህበረሰብ አቀፍ ምክክሮችን ከሚመሩና ከሚያመቻቹ አካላት ጋር ከሚካሄዱ መድረኮች አንዱ ነው ብለዋል ።

አያይዘውም ሴቶች ቤተሰብን፣ ትውልድን እና ሀገርን በኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ከመገንባት እንዲሁም ባህልንና ማህበራዊ  ዕሴቶችን ጠብቆ ለትውልድ ከማስተላለፍ አንፃር ቀዳሚ ሚና አላቸው ነው ያሉት፡፡

የምክክር መድረኩ በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ስትራቴጂዎች፣ በማህበራዊ ሀብት ግንባታ፣  በህግ የበላይነትና የዜጎች ክብር ላይ የሴቶች ሚና በሚሉ ሃሳቦች ላይ ትኩረቱን ያደርጋልም ነው የተባለው።

የምክክር መድረኩ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.