Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተላከ መልዕክት ለጂቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ አደረሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጂቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ በዛሬው ዕለት አድርሰዋል፡፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ መልዕክት ያደረሱ ሲሆን በንግግራቸውም በህውሓት ጁንታ ላይ የሚካሄደው ዘመቻ የህግ የበላይነትን በማስከበር፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን የማስጠበቅ አገራዊ ግብ ያነገበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጂቡቲው መሪ ፕሬዚደንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ ከአገራቸው ጋር በደም፣ በቋንቋና በባህል ብሎም በምጣኔ ሃብት ለተሳሰረችው ኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ አክለውም የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ መንግስት ቁልፍና በጎ ሚና የአገሪቱን ሰላም፣ አንድነትና እድገት የሚያስጠብቅ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.