Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፈረንሣይ የ15 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ፈረንሣይ ለከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን መርሃ ግብር የሚውል የ15 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሪት ያስሚን ዎሃብረቢ እና በኢትዮጵያ የፈረንሣይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ የፊርማ ስነስርዓቱን አካሄደዋል።

የተደረገው የ15 ሚሊዮን ዩሮ (669 ነጥብ 37 ሚሊዮን ብር) የሚጠጋ ድጋፍ በአዲስ አበባና በ22 መካከለኛ ከተሞች ለሚተገበረው ሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን መርሃ ግብር የሚውል ነው ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሪት ያስሚን ዎሃብረቢ የፈረንሣይ መንግስት ያደረገው ድጋፍ በከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ስለሚኖረው አስተዋጽኦ አብራርተዋል።

የፈረንሣይ መንግስት የአገር በቀል ምጣኔ ሃብት ማሻሻያውን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።

የፈረንሣይ የንግድና ገንዘብ ሚኒስትር ፍራንክ ራይስተር በስምምነቱ ወቅት በበየነ መረብ ባደረጉት ንግግር “ፈረንሣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እያደረጉት ያለውን የለውጥ ስራ ትደግፋለች” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው ሁለንተናዊ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፈረንሣይ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.