Fana: At a Speed of Life!

“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል ባቀረቡት ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመገኘት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የአስሩም ክፍለ ከተሞች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች አባት አርበኞች፣ የጸጥታ አካላት፣ መምህራንና ተማሪዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች፣ አርሶ አደሮች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሰልፍ ትርኢት አካሄደዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በያሉበት ሆነው ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር ገልፀዋል።
መርሃ ግብሩ በዛሬው እለት ከረፋዱ 5:30 ላይ በተለያዩ ስፍራዎች ለሁለት ደቂቃዎች ተካሄዷል።
በሰዓቱ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሆነው ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያ ያላቸውን ክብር ገልፀዋል።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤም በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜም በአንድነት ይቆማሉ ብለዋል።
“ኢትዮጵያውያን ተበተኑ ሲባል አንድ የሚሆኑ፤ ደከሙ ሲባሉ የሚጠነክሩ ናቸው” ሲሉም ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
“ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜም ጠንካራ ህዝቦች ናቸው ለዚህም አድዋ ይመስክር ያሉት ወይዘሮ አዳነች፥ ሉዓላዊነታችንን እስመከመጨረሻው እናስክብራለን” ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.