Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላትና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላትና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት አረጋገጡ።

“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል የ2 ደቂቃ ፕሮግራም እንዲኖር በኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የተደረገውን ጥሪ በመቀበል የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላትና ሰራተኞች አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

በምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ከጠዋቱ 5:30 ላይ በነበረው ስነ-ስርዓት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ እንዲሁም የሁለቱም ምክር ቤቶች አባላትና ሰራተኞች የተገኙተገኝተዋል።

በዚህም ሁሉም በያሉበት ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለአንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ እያጨበጨቡ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን ክብርና አጋርነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመርሐ ግብሩ ህግን ለማስከበር ተሰማርቶ ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ ላለው ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ክብር በመስጠት እንዲሁም፤ በህዝብና መንግስት የተጣለባቸውን  ግዳጅ ሲወጡ በጁንታው ሀይል ክህደት የተሰዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ተዘክረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.