Fana: At a Speed of Life!

“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ማህብረሰብ በያሉበት በመሆን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር እና አጋርነት ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለመከላከያ ሰራዊቱ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ እንዲሁም 2 ሚሊየን 286 ሺህ ብር የሚያወጡ የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍም አድርጓል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ ህግ የማስከበር ሂደቱን ተከትሎ ለቀረበው ሃገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ዩኒቨርሲቲው እንደተቋም የሚጠበቅበትን አስተዋፅዖ ለማበርከት መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተቃጣው ጥቃት እኩይ ተግባር በመሆኑ እንደሚያወግዙት እንዲሁም መንግስት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ እንደሚደግፉና የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅዖ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡
የተቋሙ የአካዳሚክ ዘርፍ ሰራተኞች የደመወዛቸውን 10 በመቶ እንዲሁም የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ደግሞ የደመወዛቸውን 5 በመቶ ለሰራዊቱ ድጋፍ እንዲደረግ ቃል ገብተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.