Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮችና ሰራተኞች በህግ የማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 9 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮችና ሰራተኞች በህግ የማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ደም ለገሱ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተገኝተው ደም ለግሰዋል።

ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ 63 ሺህ በላይ ሰራተኞች ሲኖሩት በዛሬው እለትም ሁሉም ሰራተኞች ደም በመለገስ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በደም ልገሳው ላይ የተሳተፉ ሰራተኞች የህወሓት ቡድን የሀገር አለኝታ በሆነው በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ጥቃት ሲሰሙ ከፍተኛ ሀዘን እንደሰማቸው ገልጸዋል።

ጽንፈኛውና ዘራፊው የህወሓት ቡድን በሀገር አለኝታ በሆነው በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎም ደም እየለገሱ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ሰራተኞቹ አያይዘውም መከላከያ ሰራዊትን መደገፍ ከሁሉ ነገር መቅደም ይገባልም ነው ያሉት፡፡

አያይዘውም ሀገርን ለማዳን በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ደም ከመለገስ ባለፈ በገንዘብና በሌሎች ድጋፍ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች አስፈላጊውን ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.