Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ወለጋ 142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ ወለጋ 142 የኦነግ ሸኔ ታጣዊዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ አስታወቁ፡፡
የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ 48 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ በህብረተሰቡ ውስጥ ከተበታተኑ በኋላ 64 የቡድኑ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሩ አያይዘውም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ለኦነግ ሸኔ አባላት ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 1 ሺህ 341 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ 104ቱ የህወሓት አባላት መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.