Fana: At a Speed of Life!

የጋሞ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት 6 ሚሊየን ብር እና 77 ሠንጋዎችን ለሃገር መከላከያ ሰራዊት አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 6 ሚሊየን ብር እና 77 ሠንጋ በሬዎችን አበረከቱ፡፡

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የነዋሪዎቹን ድጋፍ ዛሬ በምድር ኃይል ግቢ ተገኝተው አስረክበዋል፡፡

የዞኑ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ 6 ሚሊየን ብር፣ 77 ሰንጋ በሬዎች፣ 34 ፍየሎችና ሁለት አይሱዙ የጭነት መኪና ሙዝ ልከዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ የጀመረው የሕግ ማስከበር ሥራ በድል እስከሚጠናቀቅ ድረስም የዞኑ ነዋሪዎች ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውንም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል፡፡

ከጋሞ የሃገር ሽማግሌዎች የተወከሉት አቶ መንግስቱ ደምሴ ነዋሪዎቹ መንግስት እያደረገ ያለውን የሕግ ማስበከር ሥራ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት በመከላከያ ሚኒስቴር የሚኒስትር ዲኤታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ሲሳይ ለጋሞ ሕዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢሉ አባቦራ ዞን ሦስት ወረዳ ነዋሪዎችም ለመከላከያ ሠራዊቱ 37 ሰንጋዎችን ማበርከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተወካዮቻቸው በኩል በምድር ኃይል ቅጥር ግቢ ድጋፉን ያስረከቡት አልጌ ሳቺ፣ ዳሪሙ እና ዶረኒ ወረዳዎች ነዋሪዎች ናቸው፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.