Fana: At a Speed of Life!

ከሰዎች የበለጠ ድመቶች ያሉበት የሶሪያ ከተማ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶሪያ እና በሩሲያ ኃይሎች ለወራት ከፍተኛ የቦንብ ደብደባ ከተፈጸመ በኋላ የአማጽያን ቁጥጥር ስር የነበረችው የሶሪያ ካፍር ናባል ከተማ ከሰዎች የበለጠ የድመቶች መኖሪያ እንደሆነች ተነግሯል”

በቦምብ ድብደባ መጠለያ ያጣው የ32 ዓመቱ ሳላህ ጃር ግማሽ ደርዘን ድመቶች ጋር እንደሚኖርም ነው የታወቀው፡፡

“ድመቶቹ ቅርብ ሲሆኑ ምቾት ይሰማኛል፤ ጦርነቱን፣ ውድመቱና ሥቃዩን  በትንሹም ቢሆን ፍርሃት አንዳይሰማኝ ያደርገኛል በማለት ገልጿል፡፡

የሳላ የትውልድ ከተማ ካፍር ናብል በአንድ ወቅት ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ይሆሩባት የነበች ሲሆን፥ አሁን ከ 100 ያነሱ ሰወችና በሺዎች የሚቆጠሩ ድመቶች መኖሪያ ሆናለች።

በርካቶች በጦርነት ምክንያት ካፍር ናበል ሸሽተው በመውጣታቸው የህዝቡ ቁጥር መቀነሱም ነው የተነገረው።

አሁን ላይ ከበርካታ ድመቶች ጋር የሚኖረው ሳላፍ በአካባቢው ለሚገኝ ፍሬሽ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ በሪፖርተርነት እያገለገለ እንደሚገኝም ተነግሯል።

በማያቋርጠው የቦንብ ጥቃት ድመቶችም እንደ ሰዎች ተጎጅ ሲሆኑ አቅም በፈቀደ እነሱንም ለመርዳት ይሞከራል ይላል ሳላህ።

ሳላህ ከድመቶቹ ጋር ጥሩም፣ መጥፎም ጊዜን እንዲሁም የደስታንም የህመምና የስቃይ ስሜትንም እየተካፈሉ እንዳለ ይናገራል። በጥቅሉ የህይወት አጋር ሆነናልም ይላል።

እሱም ሆነ በካፍር ናብል የቀሩ ጥቂት ባልንጀሮቹ ከተማዋን ለቅቀው መውጣት ግድ የሚሆንባቸው ከሆነ የቻሉትን ያህል ድመቶች ይዘው እንጂ ጥለው እንደማይሰደዱ በእርግጠኝነት ይናገራል ሳላህ።

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.