Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ በአሶሳ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ ህወሓት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ፡፡

ሰልፈኞቹ ፅንፈኛና አሸባሪ የሆነው የህወሓት የጥፋት ቡድን የሀገርን ክብርና የህዝቦቿን ገናናነት የማይመጥን ክህደት ፈጽሟል ብለዋል፡፡

የጥፋት ቡድኑ ለዘመናት ሲጠብቃቸው የኖረውን፣ በሀዘን፣ በደስታና በልማት ስራዎች ከጎናቸው በመሆን ሲያገለግላቸው በኖረው የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ግፍም አውግዘዋል፡፡

መንግስት በዚህ ጽንፈኛ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን የህግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም እንደግፋለን ሲሉም አጋርነታቸውን መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.