Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለተለያዩ አካላት በወቅታዊ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ መቀመጫቸውን ናይሮቢ ላደረጉ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በወቅታዊ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጠ፡፡
በኬንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ለኩዌት፣ ናይጄሪያና ኮሎማቢያ አምባሳደሮች እና ለተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች በወቅታዊ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አምባሳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመት ከመንፈቅ መንግስት በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት የወሰዳቸውን የማሻሻያ እርምጃዎች እና የህወሓት አክራሪ የጥፋት ኃይል ይህን ለውጥ ለማጨናገፍ ሲያካሂድ የነበረውን የተለያዩ ተግባራት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አያይዘውም መንግስት የጀመረውን ህግና ስርዓትን የማስከበር እንዲሁም ህገመንግስታዊ ስርዓትን የማጽናት ተግባሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ፊቱን ወደ ልማት እንደሚያዞርም አመላክተዋል፡፡
አምባሳደሮቹና ተወካዮቹ በበኩላቸው÷ የህገመንግስት የበላይነት እንዲረጋገጥ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን የህግ ማስከበር ጥረት እንደሚደግፉ ገልፀዋል፡፡
ሚሲዮኑ ቀደም ሲል በናይሮቢ ከሚገኙ የኢጋድ፣ የዓረብ ሊግ አባል ሃገራት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ጋር ተመሳሳይ ውይይት ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ከኬንያ የመገናኛ ብዙሃን እና ናይሮቢ ለሚገኙ 30 የዓለም አቀፍ ሚዲያ ተወካዮችም ማብራሪያ መሰጠቱን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.