Fana: At a Speed of Life!

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ለጎረቤት የአፍሪካ ሃገራት ለማስረዳት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኬኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጉብኝት በማድረግ መንግስት በሕወሓት ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ለሃገራቱ ማስረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

በወቅቱም ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱንም ነው አምባሳደር ዲና የተናገሩት፡፡

ከዚህም ባለፈም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መንግሥት በቡድኑ ላይ እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ለጎረቤት ሱዳን እና ጂቡቲ ማስረዳታቸውንም ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ከዲፕሎማሲው ባሻገር ፕሪቶሪያ፣ ካምቤራ እና ዱባይ መቀመጫቸውን ያደረጉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውንም አንስተዋል፡፡

በስላባት ማናዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.