Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ዞን ነዋሪዎች እና ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊት ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወላይታ ዞን ነዋሪዎች እና ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በገንዘብና በዓይነት ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የወላይታ ዞን አስተዳደር የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችንና ተቋማትን በማስተባበር ነው 11 ሚሊየን 2 ሺህ 113 ብር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የተደረገው፡፡
ከዚህ ውስጥ 9 ሚሊየን 462 ሺህ 113 ብሩ በጥሬ ሲሆን 1 ሚሊየን 540 ሺህ ደግሞ በዓይነት ነው ተብሏል፡፡
በዚህም የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የወላይታ ሀገረ ሽማግሌዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች ተወካዮች የነዋሪዎቹንና የተቋማቱን ድጋፍ ለመከላከያ ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሎጂ አስረክበዋል።
በዚህ ወቅት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ እንደተናገሩት ÷መከላከያ ሰራዊቱ የህግ ማስከበር ተልዕኮውን እስከሚያጠናቅቅ ድረስ ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች ከጎኑ እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሎጂ የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
በማስተዋል አሰፋ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.