Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን በአዲስ አበባ ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው የህዝብ ድጋፍ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ለመከላከያ ሰራዊት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ድጋፍ ላደረጉ አካላት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየተዋደቀ ላለው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት አክብሮት፣ ድጋፍ እና ፍቅርን በተግባር በማሳየት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከ130 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ የመሪነቱን ድርሻ እንዲወስድ ላደረጉ አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ ባለሃብቶች፣ እናቶች እና መላው ነዋሪዎች የጥሬ ገንዘብ፣ የምግብ፣ የንጽህናና እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ በማድረጋቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ሰራዊታችን በህዝባዊ ድጋፍ ካልታጀበ መሳሪያ ስለታጠቀ ብቻ ብርቱ ሊሆን አይችልም ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ይህን ህዝባዊ ሰራዊት በመደገፍ የሞራል ስንቅ መስጠቱን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከከንቲባዋ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.