Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በ27 የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ፍርድ ቤት መምህርን አሰቃይቶ በመግደል የተከሰሱ 27 የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ላይ የሞት ቅጣት አስተላልፏል፡፡

የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት በቁጥጥር ስር የዋለን መምህር አሰቃይተው በመግደል ክስ ቀርቦባቸው ነው።

በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ በሌሎች አራት ተጠርጣሪዎች ላይ ከሶስት ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የፈረደ ሲሆን ሰባት ተጠርጣሪዎችን ደግሞ በነፃ አሰናብቷል።

ተከሳሾቹ በምሥራቃዊ ሱዳን ከሳላ ግዛት ውስጥ የሚሰሩ የፀጥታ ሃይሎች ነበሩ።

ዛሬ በሚጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2019 መጀመሪያ የሱዳን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽርን በመቃወም ላይ እያለ በቁጥጥር ስር የዋለው አህመድ አል ካሃር የተባለው መምህር በእስር ላይ እያለ በፀጥታ ሃይሎች በደረሰበት ስቃይ ለህልፈት ተዳርጓል።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.