የኦሮሚያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል።
የኦሮሚያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሃ ግብር ማካሄዳቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም “መከላከያ ሰራዊታችን የሀገር መከታ እና የሀገር ሉዓላዊነት ስለሆነ በምንችለው ነገር ሁሉ ከጎኑ እንቆማለን” ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ክልል የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሩ እንዳሉት፥ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን በሀገር ልማት እና ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
የኦሮሚያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን አባላት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ላሳዩት አጋርነትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።