Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በ14 ሚሊየን ብር ወጪ የአፍንጮ በር የስፖርት ሜዳ ግንባታን አስጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አፍንጮ በር ሜዳ ግንባታን ዛሬ አስጀምሯል።
ግንባታው 14 ሚሊየን ብር በጀት የተያዘለት ሲሆን÷ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ርብርብ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
የአፍንጮ በር ሜዳ 3በ1ሜዳ ፣ የፉትሳል መጫወቻ ሜዳ ፣ የሜዳ ቴኒስ ፣ሻወር እና ካፍቴሪያ እንዲሁም የዙሪያ አጥር እንደሚሰራለትም ታውቋል፡፡
የሜዳውን ግንባታ በባለቤትነት የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ሲሆን÷ ዳዊት እምሩ ህንፃ ስራ ተቋራጭ ግንባታውን ያከናውናል ነው የተባለው፡፡
ኮሚሽኑ በቀጣይም በተለያዩ አካባቢዎች የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ ግንባታ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.