Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒ ብሊንኬን በጆ ባይደን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መታጨታቸውን ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ. ሲ) አንቶኒ ብሊንኬን በተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መታጨታቸውን ይፋ አደረጉ።
እጩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባለፉት ቀናት ከስራ ባልደረቦች እና ጓደኞች የደረሱኝ መልዕክቶች ኩራትን የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል በትዊተር ገፃቸው ላይ።
በጆ ባይደን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኘ መታጨቴን ስገልፅ ኩራት ይሰማኛል ነው ያሉት አንቶኒ ብሊንኬን።
ይህ ተልዕኮ በሙሉ ልቤ የሚፈፅመው መሆኑን ላረጋገጥላችሁ አፈልጋለሁም ብለዋል።
አንቶኒ ብሊንኬን በባራክ ሁሴን ኦባማ ዘመን አስተዳደር ከፈረንጆቹ 2015 እስከ 2017 የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
እንዲሁም ከ2013 እስከ 2015 ደግሞ ምክትል የብሄራዊ ደህነነት አማካሪ በመሆን መስራታቸውም ተነግሯል።
በተመሳሳይ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው መታጨታቸውም ይፋ ሆኗል።
እጩ አምባሳደሯ በባራክ ሁሴን ኦባማ ዘመን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ነበሩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.