Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ዘመቻ ለሶማሊያው ፕሬዚዳንት ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ለሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ገለጻ አደረጉ፡፡

በዚህ ወቅትም እየተካሄደ ያለው ህግና ስርአትን የማስከበር ዘመቻ በእቅዱ መሰረት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አያይዘውም የህወሓት ጁንታ ህገ ወጥነት በቅርቡ ፍጻሜ ያገኛልም ነው ያሉት፡፡

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በበኩላቸው ሶማሊያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንደሆነች ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.