Fana: At a Speed of Life!

በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ከሁለት ሰዓት በላይ ተቋርጦ የነበረውን ኃይል በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማገናኘት ተጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ከሁለት ሰዓት በላይ ተቋርጦ የነበረውን ኃይል በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማገናኘት መጀመሩን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

ዛሬ  ከቀኑ 7 ሰዓት  ጀምሮ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በአብኛው የሃገሪቱ ክፍል ኃይል መቋረጡ ይታወቃል፡፡

ሆኖም አሁን በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ከሁለት ሰዓት በላይ ተቋርጦ የነበረውን ኃይል በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማገናኘት ተጀምሯል፡፡

ደረጃ በደረጃም  የተቀሩትን አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ የማድረግ ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.