Fana: At a Speed of Life!

ፕ/ር ቢኒያም ዳዊት ሙዝሙር በተመድ የህፃናት መብቶች ኮሚቴ አባል ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሮፌሰር ቢኒያም ዳዊት ሙዝሙር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህፃናት ኮሚቴ ውስጥ በድጋሜ አባል ሆነው ተመረጡ።
ፕሮፌሰር ቢኒያም ከፈረንጆቹ 2015- 2017 የኮሚቴው አባል የነበሩ ሲሆን በሊቀ መንበርነትም አገልግለዋል።
በተመሳሳይ ከ2013 እስከ 2015 የኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር እንደነበሩ ነው የተነገረው።
ፕሮፌሰር ቢኒያም የኮሚቴው አባል ሆነው እንዲመረጡ በጄኔቫ እና ኒውዮርክ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተለያዩ ስራዎችን ማከወናቸው ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ፕሮፌሰር ቢኒያም የኮሚቴው አባል ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.