Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በጁንታው የህወሓት ቡድን የተፈጸመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ አውግዘዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይይት ተካሂዷል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተንኳይ ጆክ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተቃጣበትን ጥቃት መክቶ ወደ ማጥቃት በመሸጋገር ድል እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገርን ለማዳን ለተሰማራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።

በዚህም በክልሉ የመንግስት ሰራተኞችና አመራሮች ደም ከመለገስ ጀምሮ የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ነው ያሉት አቶ ተንኳይ ጆክ የንግዱ ማህበረሰብም የበኩሉን ድርሻ እንድወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ፕሬዚዳንት አቶ ቸኮል በለጠ በበኩላቸው በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ልብ ሰባሪና የሀገር ክህደት ነው ብለዋል።

ወንበዴውን ቡድን ለህግ ለማቅረብ ለተሰማራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወጀለኛውን የህወሓት ጁንታ ቡድን ለህግ ለማቅረብ ለተሰማራው መከላከያ ሰራዊት ነጋዴው ማህበረሰብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ላክደር ላክባክም የንግዱ ማህበረሰብ እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.