Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ህዝብና መንግስት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ህዝብና መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት እና ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ 94 በሬዎችና 16 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሃመድ ድጋፉን ለምስራቅ ዕዝ ባስረከቡበት ወቅት፤ ሃገሪቱ ልማትና ለውጥ ላይ ባለችበት ወቅት የህወሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመው እጅግ በጣም አስነዋሪ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ጥቃቱ ከተፈፀመበት ጊዜ አንስቶ የሐረሪ መንግስትና ህዝብ ለሰራዊቱ ድጋፉን ሲገልፅ ቆይቷልም ብለዋል፡፡

ምስራቅ ዕዝን ወክለው ድጋፉን የተረከቡት የዕዙ ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ተወካይ ኮሎኔል ሃሰን ሰይድ ሃገራችን በባንዳዎች ተክዳለች፤ ጥቂት የስልጣን ጥመኞች በውስጣችን ባሉ ባንዳዎችና ከዳተኞች ተጠቅመው የሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀሙት ክህደት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የህወሓት ጁንታም በሰራዊቱና በህዝቡ ጥምረት ቅጣቱን ያገኛል እንጅ ኢትዮጵያ አትፈርስም ማለታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ህግን በማስከበር ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሀይል 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የተቋሙ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት የመከላከያሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ እየወሰዱት ላለው ህግን የማስከበር እርምጃ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.