Fana: At a Speed of Life!

የጸረ ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ”በሴቶች ላይ የሚከሰትን ጥቃት ባለመታዘዝ የብልጽግና ጉዟችንን እናስቀጥል” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ15ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ29ኛ ጊዜ የሚከበረው 16 ብርቱካናማ ጸረ ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ዋና ዓላማውም በ2030 የጾታ ጥቃትን ከዓለም ለማጥፋት ነው ተብሏል።
መርሃ ግብሩን የአዲስ አበባ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ከኢንጀንደር ኸልዝ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን÷ በዚህም ነጭ ሪቫን ለተከታታይ 16 ቀናት በማድረግ ጥቃት ሲፈጸም ዝም አልልም ጥቃትም አልፈጽምም በሚል እንደሚከበር የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሃላፊ ታደስ ግደይ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የኢንጀንደር ኸልዝ ተወካይ ጀማል ጣሰው በበኩላቸው÷ ኮቪድ-19 በዓለም ብሎም በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው የጾታ ጥቃት መጨመሩን ተናግረዋል።
በፈትያ አብደላ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.