Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል-ማህዲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 17 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል-ማህዲ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰምቷል።
ሳዲቅ አል-ማህዲ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ሆስፒታል ከገቡ ከሶስት ሳምንት በኋላ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው እና ብሄራዊው ኡማ ፓርቲ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ፡፡
በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ 21 የሚሆኑ የአል-ማህዲ ቤተሰቦች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል፡፡
የ84 ዓመቱ አል-ማህዲ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በተመራ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን እስከተወገዱበት በፈረንጆቹ 1989 ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.