Fana: At a Speed of Life!

በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ውይይት አዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ውይይት አዘጋጀ፡፡
“የኢትዮጵያን ቡና በቤልጂየምና በሉክዘምበርግ ማስተዋወቅ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ማስተዋወቂያ ዓላማ የቤልጂየምና ሉክዘምበርግ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ቡና በብዛት እንዲገዙ ለማስቻልና ቡና በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ ለማስተዋወቅ ነው ተብሏል፡፡
በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ውይይት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን፥ ቤልጂየም የኢትዮጵያ ቡና በብዛት ከሚገዙ ሃገራት ውስጥ አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዋል፡፡
የቤልጂየምና ሉክዘምበርግ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ቡና ከመግዛት በተጨማሪ በማምረቻው፣ ኢንዱስትሪ እና በቡና ማቀነባበር ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ በቡና ቢዝነስ ዙሪያ ለተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡
እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር፣ የሴቶች የቡና ማህበር እና ሶስት የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች እንዲሁም ሁለት ታዋቂ የቤልጂየም ቡና ገዥ ኩባንዎች ልምድ ማካፈላቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.