Fana: At a Speed of Life!

መርማሪ ቦርዱ የመጀመሪያውን ዙር የመስክ ምልከታ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የመጀመሪያውን ዙር የመስክ ምልከታ በማካሄድ ላይ ነው፡፡

ቦርዱ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም በጀመረው የመስክ ምልከታ እስካሁን በባህርዳር፣ በጎንደርና በዳንሻ አከባቢዎች ተዘዋውሮ የምርመራ ስራውን አከናውኗል፡፡

በከሃዲው የህወሓት ቡድን በባህርዳር እና የጎንደር አውሮፕላን ማረፊታዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በመመልከት ነው መርማሪ ቦርዱ ስራውን የጀመረው፡፡

የመርማሪ ቦርዱ አባላት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልን የጎበኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እያካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ዘመቻ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት የሰጡት እንዲሁም ቆስለው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኙት የህወሃት ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት እንደሚሉት ቀደም ሲል በህወሃት አመራሮች ከተነገራቸው ማስፈራሪያ በእጅጉ የሚቃረን እርዳታና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ለመርማሪ ቦርዱ አባላት ገልጸዋል፡፡

መርማሪ ቦርዱ ወደ ዳንሻ ባመራበት ወቅት በጽንፈኛው ቡድን የመጀመሪያው ጥቃት የደረሰበትን የሰሜን እዝ 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ጎብኝቷል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ የመስክ ምልከታውን የቀጠለ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ሌሎች አከባቢዎች ተንቀሳቅሶ መረጃዎቹን እንደሚሰበስብ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የመርማሪ ቦርዱ ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ሲባል በቅርቡ  መፅደቁ ይታወሳል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.