Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጀርስ ከዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጀርስ ከዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው  በአልጀርስ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ኃላፊ ፓውሎ ካፑቶና የኘሮጀክት ኃላፊ ከሆኑት ፍላቪያ ጂኦርዳኒ ጋር ነው የተወያዩት።

በበቆይታቸውም ኢትዮጵያውያን ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ ማግኘት በሚችሉበትና በወቅታዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ ማስከበር ዙሪያ የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በዚሁ ወቅት፥ ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ አልጄሪያ በተለያየ ምክንያት በስደተኝነት የመጡ ኢትዮጵያውያን ክብራቸው ተጠብቆና ተገቢው ድጋፍ ተደርጐላቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በዓለም ዓቀፉ ስደተኞች ድርጅት አልጄሪያ ቢሮ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የፌደራል መንግስት ሕግንና ሥርዓትን በማስከበር እንቅስቃሴው አጥፊው ቡድንና የሕወሃት ጁንታ የተቆጣጠረውን የትግራይ ክልል ዜጐች ለጉዳት ሳይጋለጡ በኃላፊነትና በጥንቃቄ  በአጭር ጊዜ ነፃ ለማውጣት መቻሉንም አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅትም በግጭቱም ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት እንዲመለሱ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ፓውሎ ካፑቶ በበኩላቸው፥ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአዲስ አበባው ዓለምዓቀፍ በስደተኞች ጽህፈት ቤት በኃላፊነት መስራታቸውን አስታውሰዋል።

ተቋማቸው በስደትና ስደት ተመላሾች ጉዳይ ዙሪያ ምንግዜም ቢሆን ዜጐች ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሁም ህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውርን ለማስቀረትም የተለያዩ ሥራዎችን እንደሚሠራም ገልፀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.